Skip to main content

 ራዕይ  

2022 በገበያ ላይ የተመሠረተ ዘመናዊ የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ሰፍኖ የአርሶ/አርብቶ/ አደሩ የኑሮ ደረጃ በመሠረታዊነት ተለውጦ ማየት፣

 

ተልዕኮ

የክልሉን እንስሳት እርባታ፣መኖ አቅርቦትና የእንስሳት ጤና አጠባበቅ በማሻሻል፣ ጥራቱና ደህንነቱ የተጠበቀ የእንስሳት ግብዓቶች እንዲቀርብና እንዲሰራጭ በማድረግ ምርትና ምርታማነት አድጎ፣የሕብረተሰቡን  ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረገገጥ የሀገር ዉስጥ ገቢና  የውጭ ምንዛሪ ማሳደግ፣

ዕሴቶች 

ኅብረተሰቡን በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ተግባራት በንቃት እናሳትፋለን!

ለአርሶ አደሩ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ቅድሚያ እንሰጣለን!

ሀብታችንን በአግባቡና በቁጠባ እንጠቀማለን!

ሙያዊ ሥነ-ምግባርን እናሰፍናለን!

ፍትሃዊነት፣ ሰብዓዊነት፣ ግልጸኝነትና ተጠያቂነትን እናሰፍናለን!

የሴቶችንና የወጣቶችን የልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን!

ቀልጣፋና ጥራት ያለዉ አገልግሎት እንሰጣለን!

ለሀገር በቀል እውቀት ዕውቅና እንሰጣለን!

የእንስሳትና ዓሳ ሀብት መረጃን ለልማት እናውላለን!

የለውጥ ኃይሎችን እንሸልማለን!

አላማ

ክልሉ በእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ እምቅ አቅም ያለዉ በመሆኑ ለሀገር ዉስጥም ሆነ ለዉጭ ገበያ ተወዳዳሮ የሆነ የእንስሳት ምርት በማምረት የክልሉን አርሶ/አርብቶ/ አደር ኑሮ ደረጃ ማሻሻልና ለውጭ ምንዛሪ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ከፍ ለማድረግ፡፡