
የሌማት ትሩፋት፣ በውጤታማ የልማት ጉዞ በሲዳማ ክልል‼ የወጣቶችን፣ የሴቶችን፣ አርብቶና አርሶ አደሮችን የአልሚዎችን ተስፋ በማለምለም፣ አንገት አስደፊውን ድህነት ለማስወገድ በቤተሰብ፣በማህበረሰብ ደረጃ ለማሸነፍ የጀመርነውን ሁሉ አቀፍ ትጋት ወደ ውጤት ለመቀየር አጋዥ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል ስሉ የሲዳማ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ተክሌ ጆንባ ተናግሯል። በሲዳማ ክልል የሌማት ትሩፋት ሥራዎች የቤተሰብ ብልፅግናን ማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ በክልላችን በሚያስገርምና በሚያስደንቅ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ኃላፊው አክሎ ተናግሯል። በሲዳማ ክልል በሌማት ትሩፋት ሥራዎችን ጉብኝት ለይ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አባላትና የግብርና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን በዳሌ ወረዳ በይርጋለም ከተማ በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝቱም በክልሉ በሌማት ትሩፋት ስራ የአርሶና አርብቶ አደሩን ተጠቃሚነትና የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ የቤተሰብ ብልፅግና ኅብረተሰብ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጥ መልኩ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችን የክልሉ ምክር ቤት አባላትና የግብርና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በክልሉ የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን ተዘዋውሮ ምልከታ ያደረጉ ሲሆን በጉብኝቱም ላይ በዘርፉ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድልን መፍጠር መቻሉን ተመልክተዋል ። በዶሮ እርባታ ፣ በከብት ማድለብ ፣ ንብ በማነብ እና በሌሎች የሌማት ትሩፋት ተግባራት ክልሉ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት በማስፋት የቤተሰብ ብልፅግናን የሚያረጋግጡ በርካታ ሥራዎች መሰራቱን በጉብኝቱ ወቅት የተገኙ ተሳታፊዎች ገልጸዋል። በጉብኝቱም ላይ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አባልና የግብርና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የሲዳማ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፍዎች እንዲሁም የክልሉ የዞንና ወረዳ የፊት አመራሮች በተገኙበት ጉብኝቱ ተካሂዷል። የካቲት 12/2016 ዓ.ም ሀዋሳ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ መግስት ኮሙኒኬሽን ። ሀዋሳ ሲዳማ ኢትዮጵያዊ