
ክልል አቀፍ ዓሣ ቀን አየተከበረ እንደሆነና በዘርፉ ሰፊ ሥራዎች እየተሰራ እንደሆነ የሲዳማ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ገለጸ። ሚያዝያ 22/2016 የቀኑ እንግዶች ዓሣን ቀን በማሰመልት በጓሮ ዓሳ ልማት የተሰሩ ሥራዎችን የጎበኙ ስሆን ባዩት ነገር ጥሩ ልምድ ልዉዉጥ እንደወሰዱም ተናግረዋል በዕለቱም ስለ ዓሳ እርባታ በክልሉ ያለዉን ምቹ ሁኔታዎችን በማስመልከት የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል እና የእንስሳት ዝርያ ማሻሻልና የእንስሳት መኖ ልማት ዘርፍ ኃላፊው ዶ/ር አደገ አለሙ ሪፖርት አቅርበዋል ። ክልል አቀፍ የዓሣ ቀን ፕሮግራም ላይ የኢፌደር ግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሣን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች እንድሁም ከየወረዳው የተወጣጡ ግንባር ቀደም ባለሙያዎችና አርብቶ አደሮች በተገኙበት ተካሂዷል። የኢፌደር ግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሣ ክልል አቀፍ ዓሣ ቀን ፕሮግራም ላይ ተገኝተው በዛሬው ቀን ክልል አቀፍ የአሣ ቀን እያከበረን ነዉ በማለት በሀገር ደረጃ ሌማት ትሩፋት ሥራ ከተጀመረ ገና 2 ዓመት ነውና እንደ ክልል በጣም ትልቅ ሥራ እየተሠራ ነው ሌሎች ክልሎችም ከዝህ ክልል ጥሩ ተሞክሮ ይወሰዳሉም ብለዋል በተጨማሪም ብዙ ወንዞችና ሀይቆች ያሉባትና ተፈጥሮ ያደላት በመሆኗ ከዝህም በላይ መሰራት እንደምቻልም ገልጸዋል። ከ2015 ዓ.ም ጀምረን በ7 ፓኬጆች ለይተን በሰራነው ሥራ ብዙ ውጤታማ ሥራ ተሠርቷል ያሉት የእንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ተክሌ ጆንባ የምመረትባቸው 3 ሐይቆች 16 ትላልቅ ወንዞች እና በርካታ ኩሬዎችና ምንጮች አሉን ለጓሮ ዓሣ ልማት የተመረጡ 14ወረዳ ስሆን ከነዚህ ውሰጥ አንዷ ይርጋለም ከተማ ናት የዛሬውን የዓሣ ቀን በማስመልከት በይርጋዓለም ከተማ የመስክ ምልከታ አድርገናል በዚህም በአንድ ወንዝ ላይ 10ኩሬ በማዘጋጀት 10 ሥራ አጥ ወጣቶች ተደራጅተው እየሠሩ ከራሳቸው አልፈው ሌለሎች 15ወጣቶች የሥራ ዕድል አንደፈጠሩና ሌላም በርካታ ሥራዎችን አይተናልም ብለዋል። በዚህ ፕሮግራም ላይ የታደሙ ከተለያዩ ወረዳዎች የመጡ እንስሳት ሀብት ልማት ጽ/ቤት ባለሙያዎችና ግንባር ቀደም አርብቶ አደሮች በጉብኝቱ ብዙ ልምድ እንደወሰዱ ተናግረዋል ። የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ መንግሰት ኮሙኒኬሽን ። ሀዋሳ ሲዳማ ኢትዮጵያ 🇪🇹