Skip to main content
y

የሲዳማ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ የእንስሳት ምጥን መኖ ተደራሽነትን ለማስፋት ከባለድርሻ አካላት ጋሪ የተደረገ የንቅናቄ ተካሂዷል። ግንቦት 23/2016 ዓ.ም የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ተክሌ ጆንባ የንቅናቄ መድረኩ ላይ ተገኝተዉ እንደ ድሮ ይሄን ያህል ከብት አለው ለመባልና የከብቶችን ብዛት ለመጨመር ብቻ ሳይሆን የተሻሻለ ዝሪያ በማርባት የተሻሌ ምርት ለማግኘት መሰራት አለብን በማለት ይህንን የእንስሳት ምጥን መኖ ዋጋ ንረትን ለማስተካከል ሲዳማ ኤልቶ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን እንስሳት ምጥን መኖ ማቀነባበሪያ ፋብርካ ጋር በመተባበር እንደምሰራም ገልጸዋል። የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ም/ኃላፊና የእንስሳት ዝሪያ ማሻሻያና የእንሰሳት መኖ ልማት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር አደገ አለሙ የ2016/17 በጀት ዓመት የእንስሳት መኖ አጠቃቀም ተደራሽነት ማረጋገጫ ሰነድ አቅርበዋል ። ሲዳማ ኤልቶ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን እንስሳት ምጥን መኖ ማቀነባበሪያ ፋብርካ የተሻሻለ እንስሳት ምጥን መኖ ማስተባበሪያ ዩኒት አሰተባባሪ አቶ ግዛቸው አማሀ ሰለ እንስሳት ምጥን መኖ አሰፈላግነትና አጠቃቀም አጠር ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት የእንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ መንግስት ኮሙኒኬሽን። ሀዋሳ ሲዳማ ኢትዮጵያ 🇪🇹