Skip to main content
y
የሲዳማ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ የሌማት ትሩፋት ሥራና የአስር (10)ወር አፈጻጸም ግምገማና ምዜና መረሃ ግብር ተጠናቋል። ቀጣይ በመድረኩ ማጠቃለያና ግንባር ቀደም መንደሮች ግንባር ቀደም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች እንድሁም ግንባር ቀደም ዞኖችን በመለየት ዕውቅናና ሽልማት የሚሰጥ ሲሆን በመጨረሻውም በሚገባ የሰሩና ያልሰሩ ወረዳዎችና ዞኖች የሚለዩበት ሥርዓት ይኖራል ተብሏል። ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሰደረግ የነበረዉ የግምገማና ምዘና መረሃ ግብሩ በዛሬ ዕለት ሰዓት በኃላ ተጠናቋል። ግምገማዉ አራቱንም ዞኖችና ሀዋሳ ከተማን ያካተተ ነበር። ሰኔ 01/2016 ዓ/ም የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የእንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዳይረክቶረት። ሀዋሳ ሲዳማ ኢትዮጵያ 🇪🇹